Telegram Group Search
ስንበሻሸቅ ተቋቁመን ስንነጋገር ወሰን ይዘን
አየሽው ፍቅራችን ተለይቶን ሲሄድብን
ስንኖር
ስንኖርር
ስንኖርርርርርርርርርርርርርር
ባላረጋገጥነው መኖራችን ውስጥ ስንት ልብ ሠበርን ስንት ነፍስ ቀጠፍን ስንት እጅ አለፍን ምን ያህል ፍቅር ገፋን መኖር ባልነው ወናፍ አኗኗራችን ስንቱን አባረን አጠፋን .....
አሁንም እንል የለ ነገ
ኖርን እያል ሶንኖር የሚያልቅ ዘመናችን አቤት ማስገረሙ .....

አደራህን ጠብቀኝ
እዚህ የሠውነት ግቢ ውስጥ ልብ አለ!!
ችፍ ችፍ ዝናም ንትርኩን ተያይዞታል አመሻሹን ቀዝቃዛ ንፋስ እየሠነጠቀው ያልፋል ስስ ጨለማ ዝናብን ተዋህዶ ሰርኩን በጊዜ አጨላልሞታል ...የኔዋ የወተት እቋዋን ይዛ እረጅም ሺቲ ከባለ ኮፍያ ሹራብጋ ለብሳ ብቅ አለች ፍንድቅ አለች ፍንድቅ አልኩ በዛ ስስ ጨለማ በነትራካ ዝናብ መሃል ተቃቀፍን ጎረሰችኝ ጎረስኳት ቀዝቃዛ ከንፈር ተቋደስን.... ሲጣፍጥ ቅዝቃዜና ሙቀት.... ከዝናብ የተዋሃደ ገፃችን ተጋጠመ የካፊያ ነጠብጣብ ያረፈባቸው ከንፈሮቻችን በተጋራነው ትኩስ ትንፋሽ አበረርናቸው አቤት ......

በዝናብ አንቺን ማቀፍ በካፊያ አንቺን መሳም
ሃጢያት ያሰርዛል ከሠማይ ከአርያም !!
ምጥጥጥጥ

እኔ አንቺ ዝናብ....

ሠብልዬን

@esubalew_sable
ስታልፊ አይቼሻለሁ ስትመለሺም እንደዛው
ታዲያ ምን ጋ ነው ይህ ልቤ የጠፋው ?
ጊዮርጊስ ጋ
ቤተል' ጋ
መሃንዲስ' ጋ
ወይራ' ጋ
ቤተሰብ' ጋ
የት'ጋ
ምኑ' ጋ
አካለልኩኝ ልከልልሽ ልከተልሽ
አንቺስ መለኛ ነሽ እንዳላይ እንዳላገኝሽ
ያንገት ማህተብሽን ትደብቂያለሽ

ሠብልዬን

@esubalew_sable
ድንቅ ነው እንደዚህ መበርታት
በመዳፍ እየገደሉ ደረትን መድቃት
ካመት እለት ቆጥሮ
ከቀንም ቀን መርጦ
ዳግም በዛው እለት ዛሬም ሊሰቅለው
በርባን ልብን ይዞ ደጀ ሰላሙን ከበበው
ቀያፋ ሆነ መንገዱ
ሀናን ሆነ አውዱ
ሰው ሁሉ ጎረፈ ወደ ጎልጎታ
ሰቀሉብኝ ላለው ለሰቀለው ጌታ
በአመል ክርፋቱ ደግሞ ደግሞ እየሰቀለው
የሡ አልታይ ብሎት ይሁዳን ኮነነው
ሺ ግዜ ሽጦ ሺ ጊዜ መድቦ በጉልት አውሎት
ሠቃይህ ጲላጦስ ነውረኛ ነው አሉት

ሠብልዬን
ሠብልዬን
@esubalew_sable
@esubalew_sable
@esubalew_sable
ፍቅር አይመለስም
ፍቅር በፍቅር ነው እሚመለሰው
ተመስገንልን አሳይተህ ለነሳሀን እንቁልልጭ እያልክ ላደከምከት ያዝነው ስንል ላስለቀከን ተመስገን
ከትትት ብለን ስቀን እንዳበቃን እንክትክት ለሚያረግ አኗኗራችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናርግ!
ቁዘማ
መኖርም ካስፈራ ...
መሞትም ካስፈራ...
የነካችኝ ሁላ እለት አየፋፋ
የዳበሠችኝ ሁላ ሠርክ እየሰፋ
አየሽልኝ አደል ተራራን ስበልጠው
ተመለከትሽ አደል ውቅያኖስን ስውጠው
ባንቺ ነው!!
ላንቺ የሚበቃ ሃገር የለም
አንቺን የሚገልፅ ሃሳብ የለም
ሁሉ ሙሉ ነው ባንቺ ሲመነዘር
"ባንቺ ሲበረበር "
አንቺን አይከት ያለም ጥልቀት
አንቺን አይበልጥ የሠማይ ርቀት
ካንቺ አይሰፋም የምድር ልብ
ካንቺ አይደርስም የአለም ግንብ
ግዘፉ ነሽ ለምድር መጠለያው
መከለያው !
ደባብሽኝ ከመኖር አዚም ልንቃ
ሙት አካሌን ለፅርቅ ላብቃ
ደባብሽኝ ሞት ይሽሸኝ በነፋስሽ ልከደን
እወድሃለው በይኝና  መኖሬንም ልመን !!

ላንቺ ነው አንቺን ነው
በረከቴ
ሠብልዬን
@esubalew_sable
@esubalew_sable
@esubalew_sable
አንጎበር ተጭኖት እንደተጨራመተ ፊት
መነቃቃት ያቃተው እሁድ ከሠአት አይነት
እሱን ሆኜ የምታየው ሱሴ አንቺን ባላይሽ ነው
ሰካራም የረገጠው ጣሳ መስዬ የምተራመሠው
በትላንቱ እኔ ውስጥ ልክ ነኝ ብዬ ልክ መሆነኔ ያንጠለጠልኩባቸው አኗኗሮቼ እና አኗኗሪዎቼ ትላንት አልፎ ዛሬ ስንሆን ቸንቧ ብለው የተበተኑ የተሰበሩ ዛሬ ደሞ ነገ የሚሰበር መኖርን እንዳበጅ ነው ወይስ እንደ ሰኞ ማክሰኞ ጨዋታ የሃሳብ ቤት መግዛት አይነት ኤክስ ምልክት አርጎ እሱን ዝለሉት ቤቴ ነው የኔ ነው እያሉ መጃጃል ነው የማይኖሩበት ክሽፈት ነገር ሲነጋ ሌላ ቤት ለመግዛት ደሞ ማነከስ መዝለል መግዛት ኤክስ ማረግ ሲነጋ ደሞ አዲስ ማነከስ

ለማንኛውም ግን ችርስ
ቸርነት ወ/ገብርኤል
2024/06/21 07:16:40
Back to Top
HTML Embed Code: